ሁለት ተቋማት ተዋህደው ኢትዮ-ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት ተመሠረተ

የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመዋሃድ ኢትዮ-ፌሪስ የባሕር የትራንስፖርት ድርጅት ተመሥርቷል።

ኢትዮ-ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት መመሥረቱ በጣና ሐይቅ ላይ ለኅብረተሰቡ እና ለጎብኚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ተመራጭ እና ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ተገኝተዋል ።

በወቅቱ በውህደቱ የተመሠረተው ኢትዮ-ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ ግንባታን ጨምሮ የትራንስፖርት፣ የጭነት እና ልዩ እንግዶች አገልግሎት የሚሰጡ ጀልባዎችን ከማስመጣት ጀምሮ በርካታ የለውጥ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል አቶ ሮባ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዴንጌ ቦሩ፣ ከተቋሙ ተልዕኮዎች አንዱ የውኃ ላይ ትራንስፖርት በመሆኑ ለአገልግሎቱ ተደራሽነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አንሥተዋል።

በውህደቱ የተመሠረተው ኢትዮ-ፌሪስ ክልሉን በቱሪዝም ዘርፍ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግን ጨምሮ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የላቀ ፋይዳ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል።

የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት በ1942 የተመሠረተ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው።

በውህደት መርሐ-ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ማሞ ምሕረቱን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.