ለሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አራት ቡድኖች መቋቋማቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል ሲል የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር መሸጋገራቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታዋ ላማዊት ካሣ በደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መሰረት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል በአፋር በኩል ካለው መንገድ በተጨማሪ ሌሎችም መከፈታቸውን ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆንም በአራት አቅጣጫ በኩል ድጋፉን የሚያስተባብሩ አራት ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ተናግረዋል።

ሰላማዊት ካሳ በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት ታጣቂ ቡድን የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከአፋር አባላ መስመር በተጨማሪ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ መስመሮች መንገዶች መከፈታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከጥቅምት 20 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአማራ እና በትግራይ እንዲሁም በአፋር እና በትግራይ አዋሳኝ አካባቢ ላሉ 316 ሺህ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተለይ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የመሰረተ ልማት አገልግሎት በፍጥነት እንዲጀመር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጦርነት ቀጠና በነበሩ አካባቢዎች የሚከናወነው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ሥራው እየተፋጠነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመብራት አገልግሎት ላሊበላ እና አካባቢው፣ ቆቦ እና አካባቢው እንዲሁም ሰቆጣ እና አካባቢው ሙሉ በሙሉ አግኝተዋል ነው ያሉት፡፡ ዝቋላ እና ዳህና ከተሞች ደግሞ በቅርቡ እንደሚያገኙ አብራርተዋል፡፡

ጥላቻን መቀስቅስ እና ልዩነትን የሚያመጡ ነገሮችን ማቆም አንዱ የሰላም የስምምነቱ አካል ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት በመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የአዘጋገብ መመሪያ ስለመዘጋጀቱም አስረድተዋል።

መመሪያው ነፃነትን ለመገደብ ሳይኾን ለሰላም ጥረቱ እንቅፋት የኾኑ ዘገባዎችን ቁጥጥር ለማድረግ የወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.