ለታዳጊ አገራት የአየር ንብረት ለዉጥ ጉዳት ማካካሻ ፈንድ ፀደቀ

በግብጽ ሻርም አልሼክ የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ተደርጓል

በ 27ኛዉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ማጠቃለያ በአየር ንብረት ለዉጡ ተጎጂ ለሚሆኑ ታዳጊ አገራት ማካካሻ የሚያደርግ ፈንድ ፀደቀ።

የበለጸጉ ሀገራት በሚለቁት ካርበን ምክንያት በሚደርሰው ብክለት ለሚጎዱ ታዳጊ አገራት ማካካሻ የሚያደርግ ልዩ ፈንድ እንዲቋቋም የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ በማጠቃለያው ወሰነ።

በግብፅ ሻርም ኤል-ሼክ ሲካሄድ የሰነበተው የአየር ንብረት ጉባዔ (COP-27) ‘ኪሳራ እና ጉዳት’ የተሰኘ ልዩ የማካካሻ ፈንድ እንዲቋቋም በማጽደቅ ተጠናቋል።

ልዩ ፈንዱ በበለጸጉ አገራት በበካይ ጋዝ ልቀት ሳቢያ በሚከሰተው የሙቀት መጨመር በታዳጊ አገራት ላይ የሚከሰተውን ጉዳትና ኪሳራ የሚሸፍን ነው ተብሏል።

በተሳታፊ አገራት ሰፊ ክርክር የተካሄደበት ይኸው ፈንድ በመጨረሻም ታዳጊ አገራት ባቀረቡት ጠንካራ የመከራከሪያ ሃሳብ አጠቃላይ ስምምነት ላይ ተደርሶ ሊጸድቅ ችሏል።

“የኪሳራ እና ጉዳት” ልዩ ፈንድ እንዲቋቋም መወሰኑ በአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት ህይወታቸው፣ ኑሯቸው እና ባህላቸው ለጉዳት የተዳረገባቸው ማኅበረሰቦችን ለመደገፍ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አወድሰዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.