በሽሬ እና አካባቢው በግዳጅ ላይ የቆየው የአማራ ልዩ ሀይል ሽኝት

የኢፌዴሪ መከላከያ በሽሬ እና አካባቢው በግዳጅ ላይ የቆየው የአማራ ልዩ ሀይል ሽኝት እንደተደረገለት አስታውቋል።

በፌዴራል መንግስትና በህወሃት አመራሮች መካከል በደቡብ አፍሪካና በኬኒያ የተደረሰውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህም መሠረት በትላንትናው ዕለት በአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች አማካኝነት ህወሃት ለመከላከያ ሠራዊታችን ከመቀሌ በ36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አጉላ ካምፕ የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሣሪያ ማሥረከቡ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ መንግስት በሽሬ እና አካባቢው ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ተሠልፎ ሀገራዊ ተልዕኮን ሲፈፅም የነበረው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል በስምምነቱ መሠረት ከቀጠናው እንዲወጣ አድርጓል።

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የዕዝ አመራሮች በተገኙበት የአማራ ክልል ልዩ ሃይል በዛሬው ዕለት ሽኝት እንደተደረገለት መከላከያ አሳውቋል።

የልዩ ሃይሉ አመራሮች እስከ አሁን የከፈልነው ዋጋ ለጋራ ሠላማችን ስንል ነውና በመንግስት ትዕዛዝ መሠረት በተደረሰው የሠላም ስምምነት ሃይላችንን ከሽሬ እና አካባቢው እያሥወጣን ነው ብለዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.