በቀላሉ ሊመረቱ የሚችሉ የፋርማሲውቲካል የፕላስቲክ ምርቶችን ከውጭ ሀገራት ይገባሉ

ኢትዮጵያ በቀላል በጀት በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ የፋርማሲውቲካል የፕላስቲክ ምርቶችን ከውጭ ሀገራት ገዝታ ታስገባለች።

በሚገርም ሁኔታ አነስተኛ የደምና የተለያዩ ናሙና መውሰጃ የፕላስቲክ ቲዩቦች ጭምር ከህንድና ከተለያዩ ሀገራት ተጭነው በኮንቴይነር ታጭቀው በየጊዜው ይገባሉ።

ይሁንና እንዚህን የፋርማሲውቲካል የላብራቶሪ ናሙና መውሰጃ ፕላስቲክ ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ማምረት የሚችል ፋብሪካዎች አሉ። ፋብሪካዎቹ ግን ምርቶቹን ለማዘጋጀት የሚያስችል የግንዛቤ ደረጃ አልፈጠሩም ሲሉ የተናገሩት አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለምሰገድ አብዲሳ ናቸው።

ዶ/ር አለምሰገድ  የፋርማሲየቲካል እንዱስትሪ ልማትን ማጠናከር የጤና ስርዓቱን ከማዘመን ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት  የፋርማሲየቲካል አምራች ኢንደስትሪ ልማት ደይሬክቶሬት አስተባባሪነት “ምርምር ልማትና ምርትን በአዲስ ምዕራፍ” በሚል መሪ ቃል የባለድርሻ አካላት ምክክር በአዲስ አበባ ሰሞኑን ተካሂዷል።

በቀላል መንገድ መመረት የሚችሉ የምርመራ ግብዓቶችን ለማቅረብ ኢንዱስትሪዎች ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተቀራርበው መስራት እንደሚችል ዶክተር አለምሰገድ  በመድረኩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ መንግስት ባዘጋጀው የ10 ዓመት ዕቅድ ትኩረት ከተሰጣቸው  ወሳኝ ጉዳዮች መካካል የፋርማሲየቲካል ኢንዱሰትሪ ልማት አንዱ ነዉ።

በዘርፉ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ጤና የሚያስፈልጉትን መድኃኒቶች በሀገር  ዉስጥ ማምረት ፣ የመመርመሪያ ኪቶችን ማዘጋጀትና  የዉጭ ምንዛሪ ለማስቀረት የሚረዳ አቅም አላት። አለባት ። በሀገሪቱ የሚከናወኑ ኢኒሼቲቮች ለምሳሌ  ኢትዮጵያ ታምርት የሚለዉ ፕሮግራም መድሃኒት ማምረትንም ያጠቃልላል ብለዋል።

 መንግስት ምርምር ልማትና ምርት በአንድ እይታ እንዲመራ ለማድረግ አዲስ ሪፎርም አካሂዷል ።በዚህ ሪፎርም መሰረት  የፋርማሲየቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ወደ አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ተቀላቅለዋል ። ስለዚህ መንግስት የሰጠንን ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የባለድርሻ አከላት ድጋፍና ትብብር አስፈላጊ  መሆኑን አንስተዋል ።

 በዚህ ምክክር መድረክ ላይ የአርማወር ሐንሰን የምርምር  ኢንስቲትዩት  ም/ዋ/ደይሬክተር  ዶ/ር አለምሰገድ  አብዲሳ   የፋርማሲየቲካል እንዱስትሪ ልማትን ማጠናከር  የጤና ስርዓቱን ከማዘመን ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

 ለዚህም ብዙ ዕድሎች እንዳሉ አንሰተዋል። እነዚህም ዐድሎች ተፈጥሮአዊ ዉጤቶች፣ የፕላስቲክ ምርቶች ፣የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የመንግስት ትኩረት መሆናቸዉን ገልፀዋል ።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.