በፈተና ውስጥ የሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በጸጥታ ችግርና በመለዋወጫ እጥረት የተነሳ ከአቅም በታች እየሰሩ መሆኑን የፌዴራል መንግስት አስታውቋል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ባሉባቸው ችግሮች የተነሳ ከአጠቃላይ ምርት አቅማቸው በ72 .4 በመቶ ብቻ እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትይረ ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ናቸው።

ኩዩና ሐበሻ ሲሚንቶ ደግሞ በፀጥታው ችግር ምክንያት ስራ ያቆሙ የሲሚንቶ ማምረቻ ፋብሪካዎች መሆናቸውም ታውቋል።

ኢስት ሲሚንቶ በበኩሉ በጥገና ስራ ላይ በመሆኑ በታህሳስ ወር ምርት እንዳላቀረበ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል።

ለሲሚንቶዎች ግብአት የሚሆን ምርት በሚመጣባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በመኖሩ ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅም እንዳይሰሩ ሳንካ መፍጠሩም ታውቋል።

በተለይ ለፋብሪካዎቹ የሚያስፈልገው የድንጋይ ከሰል የሚመረትባቸው አካባቢዎች ላይ የጸጥታው ችግር አሳሳቢነት በተቻለ ፍጥነት ጭነት የያዙ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሰቃሱ አድርጓቸዋል።

ከዚህ ባለፈ የመለዋወጫ ችግርም ያለባቸው የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መለዋወጫዎቹን ለማስመጣት የሚረዳ የውጭ ምንዛሬ በየጊዜው ሲጠይቁ ቆይተዋል።

አሁን ላይ አስፈላጊ ናቸው የሚባሉ መለዋወጫዎቻቸውን እንዲያስገቡ ለብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ መቅረቡን ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ተናግረዋል።

ችግሩ ሲፈታ የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንደሚያድግና እስከዚያው በጥቅም የተሳሰሱ የሲሚንቶ አገበያዮችን ለመለየትና ርምጃ ለመውሰድ መንግስት የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።

በእስካሁኑ የሲሚንቶ ምርት በአራት ወራት ውስጥ 1.8 ሚሊዮን ቶን በኢትዮጵያ መመረቱንም አያይዘው ገልጸዋል።

በታህሳስ ወር ብቻ 19 ሺ ቶን ሲሚንቶ ተመርቶ ለአገልግሎት መዋሉንም ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።

ሲሚንቶ በአሁኑ ወቅት እንደልብ ከማይገኙ ምርቶች መካከል መሆኑን ተጠቃሚዎች በምሬት ይናገራሉ፤ በተለይ በየመንደሩ በሚገኙ መሸጫዎች አንድ ኩንታል ሲሚንቶ እስከ 2 ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑን ኢትዮጵያን ቪው አረጋግጣለች።

በርካታ የግንባታ ስራዎች በሲሚንቶ እጥረቱና በዋጋ ውድነት የተነሳ ፈተና ላይ ናቸው፤ ይህን ችግር ለመፍታት የተጀመረው ስራ በቅርቡ ውጤት ያመጣል ተብሎ እነደሚጠበቅ መንግስት በበኩሉ እያስታወቀ ይገኛል።   

ዳንጎቴ ሲሚንቶ ኢትዮጵያ በሩብ ዓመት  837,389 ቶን ለማምረት አቅዶ 837,993.21 ቶን ከእቅዱ በላይ በማምረት 100.31 ፐርሰንት አፈጻጸም አስመዝግቧል ፡፡

በአንጻሩ ሙገር ሲሚንቶ በሩብ ዓመቱ 300,320 ቶን ሲሚንቶ ለማምረት አቅዶ 159,630 ቶን በማምረት ማሳካት የቻለዉ የዕቅዱን 53.15 በመቶ ብቻ ነዉ፡፡

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.