በ106 አንቀጾች የተዋቀረው ህገመንግስቱና ማሻሻያው

የኢትዮጵያ ህገመንግስት በ11 ምዕራፎችና በ106 አንቀጾች የተዋቀረ ነው።

ህገመንግስቱ በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት የጸደቀ ሲሆን፤ በመግቢያው ላይ ይህ ሕገ መንግሥት ከዚህ በላይ ለገለጽናቸው ዓላማዎችና ዕምነቶች ማሰሪያ እንዲሆነን እንዲወክሉን መርጠን በላክናቸው ተወካዮቻችን አማካይነት በህገ መንግሥት ጉባኤ ዛሬ ኅዳር 29 ቀን 1987 አጽድቀነዋል የሚል ጽሁፍ ሰፍሮበታል።

በተለያየ ጊዜ ግን ህገመንግስቱ መሻሻል እንዳለበት ጽድጽ የሚያሰሙ ወገኖች መኖራቸው አልጠፋም። ህገመንግስቱ ከህዝብ ፍላጎትና ከወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ተቃሽቶ መሻሻል እንዳለበት የተለያዩ ምሁራንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሲጠይቆ ቆይተዋል።

ሕገ መንግስቱን ማሻሻል የሚቻልበት አሰራር በራሱ በሕገ መንግስቱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።  በህገመንግስቱ አንቀጽ 104 የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳብን ስለማመንጨት ተደንግጓል።

በድንጋጌው ላይ አንድ የህገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የደገፈው፣ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የደገፈው ወይም ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የክልል ምክር ቤቶች በድምጽ ብልጫየደገፉት ከሆነ ለውይይትና ለውሳኔ ለመላው ሕዝብና የህገ መንግሥቱ መሻሻል ለሚመለከታቸው ክፍሎች ይቀርባል ይላል።

ህገመንግሥቱን ስለማሻሻል በሚያትተው ድንጋጌ አንቀጽ 105 ንጹስ አንቀጽ 1 ላይ ደግሞ

ሀ/ ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምጽ ብልጫ ሲያጸድቁት፣
ለ/ የፌዴራሉ መንግሥት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቀው፣ እና
ሐ/ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ማሻሻያውን ሲያጸድቀው ነው፡፡


2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉት የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኋን ብቻ ይሆናል፤
ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት፣ እና
ለ/ ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎቸ ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምጽ ብልጫ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት ነው በሚል ሰፍሯል።

ዛሬ ደግሞ በሒልተን ሆቴል አዲስ አበባ በተሰናዳ መድረክ “ሕገመንግስቱ ከሦስት አስርት ዓመታት በኃላ ሊሻሻል ይገባል ወይ? ከሆነስ ምን ምን ላይ ይሻሻል?” በሚል ርዕስ የተካሄደ የጥናት ግኝት ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

የጥናቱ ትኩረት ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ጥናቱን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።

አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ በውይይቱ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ላለፉት ሁለት ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን ገልጿል።

ሕገ መንግሥቱ ከረቀቀበት 1987 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች መነሻ እራሱ ሕገመንግስት ነው የሚሉ ሃሳቦች  በተለያዩ ጊዜ ሰሲነሱ እነደነበር አስረድተዋል።

ሀሳቡን መነሻ በማድረግ በሕገመንግስት ማሻሻያዎች ዙሪያ ጥናት መከናወኑን ተገልጿል።

ለጥናቱ መነሻ ከትግራይ ክልል ውጪ ባሉት ሁሉም አከባቢዎች መሰብሰቡንና  በጥናቱም በ2000 ዓ.ም በሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት ሲስተማቲክ ራንዶም ሳምፕሊንግ (systematic random sampling) መመረጣቸውን ነው የተናገሩት።

በዚህም መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣ ብሔራዊ አርማ፣ ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣ መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣ የፖለቲካ ፓርቲን በብሔር ማደራጀት እና የአዲስ አበባ አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው ሕዝቡ ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል።

የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ባቀረቡት የመነሻ ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ሕገ-መንግሥቱ ከተረቀቀበት ጊዜ አንሥቶ ክርክር እየተነሣበት እንደሚገኝ አስረድተዋል።  

ሕገመንግስቱ በርካታ አከራካሪና ለግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች መያዙን ነው የተናገሩት።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን በበኩላቸው፣ ሕገመንግስቱ በጭራሽ መሻሻል የለበትም ፤ ህገ መንግስቱ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መተካት አለበት እና ጥናትን በተከተለና በአካታች ውይይት ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል የሚሉ ዋና ዋና እሳቤዎች እንዳሉ የጥናቱ ግኝት ማመላከቱን ገልጸዋል።

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ዘሃራ ዑመድን ጨምሮ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ኃላፊዎች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.