በ5 ዘርፎች ያሸነፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የባህር ወደብ የሌላት የምስራቅ አፍሪካዋ ኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ ገቢዋን ለማሳለጥ በጂቡቲ ወደብ ብትጠቀም ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሌላኛው የመውጫ መግቢያ አማራጭ ሆኖ እያገለገላት ይገኛል።
በተደጋጋሚ ብቃቱን ያስመሰከረው አየር መንገዱ በአንድ አመት ከ6.1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢን በማስገባት የማይተካ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።
አየር መንገዱ በተደራጀ አመራርና ባለሙያዎች የተዋቀረ በመሆኑ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎቱን ለማግኘት ከአሜሪካ እስከ እስያና አውሮፖ ፈላጊዎቹ ብዙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አስመስክሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገዱ እንደለመደው ሁሉ በአገልግሎቱ የአፍሪካ ሀገራትን ቀድሞ መገኘቱን በተለያዩ መድረኮች ዕውቅና ተበርክቶለታል።
አሁንም በዓመታዊው የ ” SKYTRAX ” ውድድር ላይ በ5 ዘርፎች ሽልማት አግኝቷል።
አየር መንገዱ አሸናፊ የሆነባቸው ዘርፎች ፦

1.” Best Airline in Africa 2023 ” ለተከታታይ 6ኛ ጊዜ፣
2.” Best Business Class Airline in Africa 2023 ” ለተከታታይ 5ኛ ጊዜ፣
3.” Best Economy Class Airline in Africa 2023 ” ለተከታታይ 5ኛ ጊዜ፣
4.” Best Business Class Onboard Catering in Africa 2023 ” ለተከታታይ 2ኛ ጊዜ
5.” Cleanest Airline in Africa 2023 ” ዘርፎች ናቸው።

አየር መንገዱ ሽልማቶቹን በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው ” Paris Air Show ” መርሐ ግብር ላይ ተቀብሏል::

netevm.com