የቱርክ ሐኪሞች በልብ የሕክምና ዘርፍ ከኢትዮጵያ ሐኪሞች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ

በልብ የሕክምና ዘርፍ የረጅም ዓመት ልምድና ዕውቀት ያላቸው የቱርክ ሐኪሞች ኢትዮጵያ ሐኪሞች ጋር በአዲስ ከበባ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

ጌትዌል ሜዲካል ትራቭል በቱርክ ከሚገኘውና በተራቀቀ ቴክኖሎጂ ከሚታወቀው አቺባደም ሆስፒታል ጋር በመተባበር አንጋፋ የሆኑትን የአቺባደም የልብ ሀኪሞች እና የልብ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞችን ወደ አዲስ አበባ አስመጥቷል።

ሐኪሞቹ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በዘርፉ ሕክምና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጡ ታውቋል።

አቺባደም ሆስፒታል በዓለም ላይ በጠቅላላ ከ22 በላይ ሆስፒታሎች ያሉት ሲሆን በኢትዮጵያም ቢሮውን በመክፈት በጤናው ዘርፍ ማህበረሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችም ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ ከተለያዩ አገር የተወጣጡ ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኒታዎችን እየፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

ሰባተኛ የሆነውን የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ አድርጓል። በእለቱም የአቺባደም አታከንት ባልደረቦች በሕክምናው ዘርፍ ያሉ አዳዲስ ጥናቶችን በሀገራችን ለሚገኙ ሐኪሞች አቅርበዋል።

ጌትዌል ሜዲካል ትራቭል የጤና ማማከር እና የውጭ ሀገር ህክምና በ4 ሀገራት ካሉ የህክምና ተቛማት ጋር በአጋርነት በመስራት የሕክምናና የጉዞ ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑ ተገልጿል።

ጌትዌል ሜዲካል ትራቭል የጤና ማማከር እና የውጭ ሀገር ህክምና ልምድ ካላቸው ህንድ፣ ቱርክ፣ዱባይ እና ታይላንድ ከሚገኙ ከፍተኛ የህክምና ተቛማት ጋር በአጋርነት እየሰራ ይገኛል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.