አለም አቀፍ የበይነ መረብ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተጀመረ

ጉባኤው በኢሲኤ አዳራሽ እየተካሄደ ነው

ኢትዮጵያ 17ኛውን ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ማስተናገድ ጀምራለች።

የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከበይነ-መረብ ጋር ተያይዞ ያሉ ዕድሎችን እንዲሁም ፈተናዎችን በተመለከተ የሚነሱ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበትና የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የመነሻ ሃሳብ የሚገኝበት የውይይት መድረክ ነው፡፡


የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን የጉባኤው አዘጋጅ መሆን ቢቃወሙም መሰናዶው ላይ የጎላ ተጽዕኖ ሳያስከትል መድረኩ ዛሬ ተጀምሯል።


“የበይነ መረብ የመቋቋም ችሎታ ዘላቂነት ላለው የጋራ የሆነ የወደፊት እድገት (Resilience internet for a shared sustainable and common future) በሚል መሪ ሃሳብ ከህዳር 19 እስከ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ይቀርቡበታል ።


ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።


የበይነ-መረብ አስተዳደር ፎረም የተለያዩ ጉዳዮች በህግና በሌሎች ማዕቀፎች የሚፈቱበት አግባብ የሚመላከትበት ጉባኤ ነው፡፡


ጉባኤው አስገዳጅ የሆኑ ውሳኔዎች የሚወሰኑበት ሳይሆን ውሳኔ አመንጪና ሰጪ የሆኑት የግሉን ዘርፍና መንግስትን በጉዳዮቹ ላይ የመረጃ ና የፖሊሲ ሀሳብ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡


ጉባኤው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አማካኝነት እኤአ በ2006 ዓ.ም. ይፋ የተደረገ ፎረም ነው፡፡


በመድረኩ አስገዳጅ የሆኑ ውሳኔዎች የሚወሰኑበት ሳይሆን ውሳኔ አመንጪና ሰጪ የሆኑት የግሉን ዘርፍና መንግስትን በጉዳዮቹ ላይ የመረጃ ና የፖሊሲ ሀሳብ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡


ፎረሙ ለመጀመሪያ ጊዜ እኤአ በ2006 በአቴንስ፣ ግሪክ ከተደረገ በኃላ እስካሁን ድረስ 16 ግዜ በተለያዩ ሀገራት ተካሂዷል። 17ኛው ፎረም ደግሞ ህዳር 2015 በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡ በቀጣይ ህዳር ወር ኢትዮጵያ በምታካሂደው ጉባኤ አምስት አብይት ጭብጦች ላይ ይመክራል።


ከበይነ-መረብ ግንኙነት ውጪ የሆኑ ህዝቦችን ማገናኘትና ሰብዓዊ መብትን መጠበቅና ሰዎችን ከጥቃት መከላከልና. ዳታን በአግባቡ ማስተዳደርና የግል ዳታ ጥበቃ ላይ ውይይት ይደረጋል።


የተከፋፈለ የኢነትርኔት አገልግሎትን መቅረፍና የደህንነትን ማረጋገጥ፣ ጥበቃ ማድረግና ተጠያቂነትን ማስፈን እንዲሁም የመጪ ግዜ ቴክኖሎጂዎች የሆኑትንና እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ያሉ ጉዳዮች ይነሳሉ፡፡


ኢትዮጵያ 17ኛውን የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ እንድታዘጋጅ የተመረጠችበት ምክንያት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተለያዩ ለውጥና እድገቶች እያስመዘገበች መሆኗ አንዱ ምክንያት ነበር።


ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ፣ በቴሌኮም ዘርፍ የተለያዩ የማሻሻያዎች በማድረግ ዘርፉን ለአለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች ክፍት ማድረጓ እና የቴሌኮምና የበይነ-መረብ ተደራሽነትን ለማሳደግ እያደረገች ባለው ጥረት ታይቷል፡፡


ኢትዮጵያ ከ60 ሚሊየን በላይ ሞባይል ተጠቃሚያላትና ከ20 ሚሊዮን በላይ የበይነመረብ ተጠቃሚዎች መኖራቸው አዘጋጅ ሀገር ሆና እንድትመረጥ አስችሏታል።


አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ባለፉት ጊዜየት የኢትዮጵያን የጉባኤው አዘጋጅነት ክፉኛ ሲተቹ ነበር። ሬውተርስ ኢትዮጵያ ከጦርነት ጋር በተያያዘ በትግራይ ክልል ስልክና ኢንተርኔት መዝጋቷን አንስቶ የጉባኤው አዘጋጅ መሆኗ እንደማይገባ አትቷል።


በርካታ የምዕራቡ አለም መረጃ አቅራቢዎች የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት እቀባን በተለያዩ ጊዜያት እንዳደረገ በማንሳት ሲተቹ ቆይተዋል።


ይሁንና ኢትዮጵያ እንግዶቿን ተቀብላ ጉባኤውን በአማረ ሁኔታ አስጀምራለች።
በጉባኤው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ሊ ጁንሁዋ፣ የፓፓዋ ኒው ጊኒ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ቲሞቲ ማሲዩ፣ የኢንተርኔት አባት በመባል የሚታወቁት ቪንቶን ግሬይሰርፍን ጨምሮ ከሦስት ሺ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።


ይህ ጉባኤ በበይነመረብ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ያተኩራል ተብሏል።
16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ “ኢንተርኔ ለአንድነት (Internet united)” በሚል መሪ ቃል ባለፈው አመት በፖላንድ መካሄዱ የሚታወስ ነው።


የ17ኛው ጉባኤ ተሳታፊዎች የሳይንስ ሙዚየምንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.