ከ79ሺ ቶን በላይ ቆሻሻ በየዓመቱ የሚሰበሰብ ሲሆን ከዚህ ውሰጥ ከ67ሺ ቶን በላይ የሚሆነውን መልሶ መጠቀም መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።
ከ67ሺ ቶን በላይ የሚሆነው ቆሻሻ የፕላስቲክ ፣ የወረቀት ፣ የምግብና የተለያዩ ተረፈምርትን ያጠቃለለ ነው።
በመዲናዋ ከሚመረተው ቆሻሻ እስከ 75 በመቶ የሚሆነው የሚበሰብስ በመሆኑ ወደ ኮምፖስት የመቀየር ሥራ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ከቆሻሻ መልሰን ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ፕላስቲኮች፣ ወረቀቶች፣ ብረቶች ፣ ጠርሙሶች ፣ ወዘተ ጥቅም ላይ በማዋል የተለያዩ ዜጎች ገቢ እያገኙ ነው።
ቆሻሻን በፍተኛ ኃይል በማቃጠል ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ይውላል ፣ በሀገራችን በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው 25 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመጠነኛ አቅም እየሠራ ነው።
ሌላው በመቅበር በሚወገድበት ጊዜ ዝቃጮች ታክመው፣ መርዛማ ከሆኑ የማስተንፈስ ሥራ ጤናን በማይጎዳ መልኩ እንደሚከናወን ተቋሙ ገልጿል።
ቆሻሻ መጣያ የነበሩ ስፍራዎችን በማጽዳት የተለያዩ ዕፅዋት አበባዎች እየተተከሉባቸው ውብ እየሆኑ መምጣታቸውን ታይቷል።
ቆሻሻ ሀብት በመሆኑ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ እየፈጠርን ቆሻሻን የሚጸየፍ እና በአግባቡ የሚያስወግድ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል ሲል ኤጀንሲው ገልልጿል።