ኢቢጂ ያስመጣቸውን የ FAW ተሽከርካሪ ምርቶች አስተዋወቀ

ኢኳቶሪያ ቢዝነስ ግሩፕ (ኢቢጂ) ከተሰማራባቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ያስመጣቸውን የ2023  ኤፍኤደብሊው (FAW) አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የጭነት መኪኖች ለደንበኞቹ አስተዋወቀ፡፡

መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ስነስርዓት የኢቢጂና የ FAW  ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አማካሪና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የተሽከርካሪ ማስተዋወቅ ስነ-ስርዓት የ FAW  ምርቶች ከሆኑትና በኢቢጂ ለአገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎች መካከል ከፍተኛ የጭነት አቅም ያለው ከልባጭ ተሽከርካሪ ትኩረት ስቦ ነበር።

ተሽከርካሪው በውስጡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለትና የተሽከርካሪዎችን ደህንነትና ምቾት ለመጠበቅ የሚረዳ አልጋ የያዘ መሆኑ በወቅቱ ተገልጿል።

በዕለቱ የቀረቡ የተለያዩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ አየር ንብረትና መልከአምድር የሚስማሙ መሆናቸው ተመላክቷል።  

የFAW ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ ለማስመጣት ፍቃድ ያገኘው ኢቢጂ ከዚህ ቀደም ከተሽከርካሪ አምራች ድርጅቱ ጋር በመሆን ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያገኙ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት ተሽከርካሪዎቹን የሚወስዱ ደንበኞች አስፈላጊው የጥገና አገልግሎትና የመለዋወጫ ዕቃዎችን የሚያገኙበት አማራጭ መመቻቸቱ ተገልጿል።

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ አይነት ተሽከርካሪዎችን አገር ውስጥ አስመጥቶ በማከፋፈል ልምድ ያለው ድርጅት ነው።

 

netevm.com