ኢትዮጵያና የብሪክስ አባልነት ፋይዳ

ስለ BRICS ምን ይታወቃል፤ ዓላማውስ ምንድነው ?

  • BRICS አሁን ላይ አዳዲስ አባል ሀገራትን ሳይጨምር የተመሰረተው እኤአ 2001 ላይ በብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣  ቻይና  ነው። በኃላም ደቡብ አፍሪካን አካቷል።
  • የምዕራባውያን ተፅእኖን ለመገዳደር የተመሰረተ ስብሰብ ነው። በተጨማሪ እንደ IMF እና ዓለም ባንክ ያሉ የገንዘብ ተቋማትን አሰራር የማሻሻያ መንገዶችን ለመፈለግ፣ ለታዳጊ አገራት ምጣኔ ሃብት ድምጽ እና ውክልና ለመፍጠር ነው።
  • አባል ሀገራቱ የቡድኑ አላማ ፍትህ እንደሆነ እና ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት እንዲፈጠር መስራት መሆኑን ይናገራሉ። በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የዓለም ስርአት እንዲያከትም ይፈልጋሉ።
  • አሁን ይቀላቀለሉ የተባሉ አባል ሀገራትን ሳይጨምር አምስቱ ሀገራት ብቻቸውን 3.24 ቢሊዮን የህዝብ ብዛት አላቸው። ያላቸው ብሔራዊ ገቢም አንድ ላይ ሲሰላ 26 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህ ከዓለም ምጣኔ ሃብት 26 በመቶውን የሚይዝ ነው።
  • የBRICS አባል ሀገራት ለዓለም ንግድ #ከዶላር ውጪ ተጨማሪ መገበያያ ገንዘብ መኖር እንዳለበት ያምናሉ።
  • ለዓለም ንግድ ዋነኛ መገበያያ ከሆነው ዶላር ተጨማሪ የመገበያያ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የሚያምኑት አባል ሀገራቱ ዓለም በጥቂት ሀገራት የበላይነት መመራቷ ማብቃት አለበት የሚል የፀና አቋም አላቸው።
  • የኢኮኖሚ የበላይነቱ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ መወሰኑ ብዙ ሀገራትን በጥቂቶች ጫና ስር እንዲወድቁ በማድረጉ ይህን ለማስተካከል እንደሚሰሩ አባል ሀገራቱ ይናገራሉ።

የብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ ፣ ቻይና እና ደ/አፍሪካ ስብስቡ BRICS ” ልንቀላቀላችሁ እንፈልጋለን ” ብለው ጥያቄ ካቀረቡለት ሀገራት መካከል በነዳጅ ሀብታም የሆኑትን ኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን ጨምሮ ኢራን፣ ግብፅና አርጀንቲናን በመጨመር እና አባል እንዲሆኑ በማፅደቅ አጠቃላይ የአባል ሀገራቱን ስብሰብ ወደ 11 አሳድጓል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ትገኛለች ። በተለይ ቻይናና ሳውዲ ባሉበት ብሪክስ ከአሜሪካ ዶላር ይልቅ የየሀገራቱ ገንዘብ አሊያም አንድ ወጥ ገንዘብ በማሳተም እርስ በእርስ የሚገበያዩበት መንገድ ወደፊት ሊፈጠር እንደሚችል የዘርፉ ምሁራን ይጠቁማሉ።

የውጭ ምንዛሪ እጥረት ላለባት ኢትዮጵያ ይህ ታላቅ ብስራት ነው። ከዚህ ባለፈ የፖለቲካዊና ወታደራዊ ጥምረቶችን ሊመሰርቱ የሚችሉበት ዕድል በመኖሩ የኢትዮጵያን አቅም በቀጣናው እንደሚያሳድገው ይገመታል።

netevm.com