ኢትዮጵያ ለዲፕሎማቶቿ የሰጠችው ስልጠና ተጠናቀቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋና መሥሪያ ቤት እና በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን ወክለው ለሚሠሩ ዲፕሎማቶች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቅቋል።

በሱሉልታ ከተማ የአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ውስጥ ለሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና ባለስልጣናት በተሰጠው ስልጠና የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ ይዘትን እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ አሰላለፍን የተመለከተ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች ቀርበውበታል።

ሥልጠናው የመዝጊያ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ባስተላለፉት መልእክት፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ፣ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በዚህ ዘመን ምን ዓይነት ቅርፅ እና ተሳትፎ ሊኖር ይገባል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለዲፕሎማቶች ሥልጠና ሰጥተዋል።

የዓለም ሁኔታ ውስብስብ፣ ተገማች ያልሆኑ የአሰላለፍ የተለያዩ ፍላጎቶች በዓለም አቀፍ ግንኘነት እና ዲፕሎማሲ በመኖሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ተደማጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንዲኖር ለማስቻል ዲፕሎማቶች በዕውቀትና በክህሎት ራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ወደፊት በሚደረገው የውጭ ግንኘነት የማሻሻያ ፍኖተ ካርታ እንዲሁም የመልሶ ማደስ እንቅስቃሴ በተግባር የኢትዮጵያን በአዲስ ገፅታ የማስተዋወቅ ሠራ የሚሠራበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

አቶ ደመቀ በሥልጠናው ማጠናቀቂያ በሰጡት የሥራ መመሪያ የኢትዮጵያን በመወከል በሚደረጉ በሁሉም የዲፕሎማሲ ስምሪቶች የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ይበልጥ ዲፕሎማቶች በንቃት መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።

ሥልጠናው ዲፕሎማቶቹ አሁናዊ የሆነውን ተለዋዋጭ፣ ተገማች ያልሆነውን እና የተወሳሰበውን የዓለም ሥርዓት በማንበብ የሀገራቸውን እውነት እና ጥቅም ማስከበር እንዲችሉ የሚያገዝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሥልጠናው የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ በብቃት የሚያከናውን ዲፕሎማት ለመፍጠርም ሰፊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተግባሯን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም በሰው ኃይል ልማት ይበልጥ እየሠራች መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሚኖራትን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ ከዚህ የበለጠ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራም ተገልጿል።

የአገሪቱ የዲፕሎማሲ ጉዞ በለውጥ እና በተፈተናዎች የታጀበ በመሆኑ ይህን ለመመከት ራስን ከሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ፣ ከአዝማሚያዎች ጋር ራስን ማብቃት እንደሚገባም ተገልጿል።

ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ወቅቱን ያገናዘበ እና በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

በማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ይልማ የተገኙ ሲሆን ለሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.