ኢትዮጵያ የ2 ቢልየን 6 ቢልየን ዶላር የንግድ ክፍተት አጋጠማት

ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ሶስት ወራት የ2 ቢልየን 623 ሚሊየን ዶላር የወጭና ገቢ ንግድ ክፍተት እንዳጋጠማት ታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ በምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ፊት ቀርበው አጠቃላይ ስለኢኮኖሚው ሁኔታ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ወደ ውጭ አገራት የላከቻቸው ምርቶች 977 ሚሊዮን ዶላር  ገቢ እንዳስገኙ ገልጸው፤ በአንጻሩ አገሪቷ የ3.6 ቢልየን ዶላር ወጪ ማድረጓን አስረድተዋል።

ወደውጭ ከተላኩት ምርቶች ውስጥ አበባና ቡና ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ የተናገሩት ዶክተር ይናገር ደሴ የወርቅ ምርት ግን ባለፈው አመት ሶስት ወራት ከነበረው አንጻር በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ነው ያሳወቁት።

የወርቅ ምርት የሚመረትባቸው አካባቢዎች ላይ የጸጥታ ችግር መኖሩን በመግለጽ፤ በተጨማሪ ቻይናዎች ጭምር የተሳተፉበት የህገወጥነት ስራ መኖሩንም አንስተረዋል።

አሁን ላይ ቻይናዎቹን ከማሰር በተጨማሪ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ ምርት ባለፉት ሳምንታት መጨመር መጨመሩን ተናግረው፤ በምን ያክል መጠን እይጨመረ መሆኑን ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በተያያዘ ኢትዮጵያ ካወጣችው የውጭ ምንዛሬ ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው የነዳጅ ምርት ለማስገባት የተከፈለው መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ከውጭ በርካታ ምርቶችን የምታስገባና ወጪዋም ከፍ ያለ ነገር ግን ወደውጭ የምትልካቸአው ምርቶች ደግሞ አነስተኛ መሆናቸው ይታወቃል።

የወጪና ገቢ ንግድ ክፍተቱ ሲሰፋ መንግስት ላይ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ጫና ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል።

መንግስት በስንዴ ምርታማነት ላይ እያከናወነ ያለው ስራ በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጭምር የተደነቀ ቢሆንም የጸጥታ ችግሮች ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያለው ምርታማነቱን እንዲቀንስ አድርጓል።

ዶክተር ይናገርም በቀጣይ ጊዜያት ኢትዮጵያ ምርቶችን በብዛት ወደውጭ መላክና የምንዛሬ አቅሟን ማሳደግ እንዳለባትም አስታውሰዋል።

ለዚህ ስራ እያንዳንዱ ክልለና ተቋማት አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው የባንኩ ገዥ አሳስበዋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.