ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ (ፔሌ-Pele)

በሙሉ ስሙ ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ በመባል የሚታወቀው ፔሌ በብራዚል ጥቅምት 23 ቀን 1940 ተወለደ። ያደገው በድሃ ቤተሰብ ውስጥ ነው።

ከልጅነቱ ጀምሮ እግር ኳስ ጨዋታን ይወድ ነበር። አባቱ ጆአዎ ራሞስ ዶ ናሲሜንቶ እግር ኳስ ተጫዋች ናቸው።

ገና በለጋ ዕድሜው ኳስ እንዲጫወት ያበረታቱት ነበር። ባለተሰጥኦው ፔሌ የአባቱን ምክር እየተከተለ ጥበበኛ ካስ ተጫዋች ለመሆን ብዙ አልተቸገረም።

ተፈጥሮውና ድንቅ ብቃቱ ታክሎበት የእግር ኳስ አድናቂዎችን ቀልብ የሳበው በመንደሩ በሚገኙ አነስተኛ ሜዳዎች ላይ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ነው።

ፔሌ የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ኮንትራት በተወለደባት ብራዚል ከሳንቶስ እግር ኳስ ክለብ እ.ኤ.አ. በ1956 ተፈራርሟል። በወቅት ገና የ15 ዓመት ዕድሜ ላይ ነበር።

ፔሌ  1,281 ጎሎችን በማስቆጥር በዓለም ክብረ ወሰኑን አሁንም የያዘ ሲሆን፣ የዓለም ዋንጫን ሶስት ግዜ በማንሳትም ብቸኛው ተጫዋች ነው።

“የእግር ኳሱ ንጉስ’’ ተብሎ የሚጠራው ብራዚላዊው ኳስ ተጫዋች ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ፔሌ ካገኛቸው ክብሮች መካከል –

– እ.ኤ.አ በ 1999 የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የምተዓመቱ ስፖርተኛ

– እ.ኤ.አ በ 2000 የአለም አቀፍ እግር ኳስ እና ታሪክ የምትዓመቱ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች

የእግር ኳስ የበላይ አካል ፊፋ ፔሌን ታላቁ ተጫዋች ሲልም እንደሚገለፅው ይታወቃል።

እ.ኤ.አ በ 1940 የተወለደው ፔሌ እግር ኳስ ገና በልጅነቱ በአስራ አምስት ዓመቱ በሳንቶስ ክለብ በመጫወት መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

ለሃያ አንድ ዓመታት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫውቷል። ሠላሳ ሁለት ሻምፒዮናዎችን ያሸነፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ የዓለም ሻምፒዮናዎች ናቸው። ዘጠና ጊዜ ሃትሪክ ሰርቷል፣ በሰላሳ ግጥሚያዎች ላይ በእያንዳንዱ ጨዋታ አራት ጎሎችን አስቆጥሯል። 

ፔሌ በአለም ዋንጫ ታሪክ ሶስት የዓለም ዋንጫዎችን፣ በ1958፣ 1962 እና በ1970 ከሀገሩ ጋር የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ብቸኛ ባለታሪክ ነው፡፡

በ1958 የፔሌ የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ድል ገና 17 አመት ከ 249 ቀን ሲሆነው ሲሆን ይህም ውድድሩን ያሸነፈ ትንሹ ተጫዋች አድርጎት ነበር።

ባለፈው አንድ ወር በአንጀት ካንሰር ሳቢያ ህክምና ሲደረግለት የቆየው ፔሌ ባለፈው ሣምንት አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ሰውነቱ ለካንሰር ህክምና ምላሽ መስጠት ካቆመ በኋላ ወደ ህክምና ተወስዷል። ቤተሰቦቹን በሳኦ ፓውሎ በሚገኘው በአልበርት አንስታይን የእስራኤል ሆስፒታል የተሰናበተውም ከሳምንት በፊት ነው።

አሁን ፔሌ አርፏል። በርካታ አድናቂዎቹም የሃዘን መገለጫቸውን እያወጡ ነው። እንቁ ተጫዋች ታሪኩን አሳርፎ አሻራውን ጥሎ አልፏል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.