ከሀገር ውስጥ የስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ 109 ኤጀንሲዎች ታገዱ

ከሀገረው ስጥ የስራ ስምሪት ጥፋት ጋር በተያያዘ የ109 የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የስራ ፈቃድ መሰረዙን የአዲስ አበባ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ርምጃ የተሰወደባቸው ኤጀንሲዎች በሀገር ውስጥ ሰራተኞችን በማገናኘት ላይ የሚሰሩ መሆናቸው ነው የተመላከተው።

የመዲናዋ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ  ምክትል ሃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ የተለያዩ ዜጎች በአገር ውስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

ቅሬታውን መነሻ በማድርግ በተደረገ ቁጥጥር ችግሩ የተገኘባቸው በተለይም ገንዘብ ወስደው ስራ የማያገናኙ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው አላግባብ ሰራተኞችን የሚያጭበረብሩና የተለያየ ችግር የተገኘባቸው ኤጀንሲዎች ተዘግተዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ  የአሰሪና ሰራተኛ ቅጥር ህጋዊ መስፈርትን ሳያሟሉ በዘፈቀደ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንደተደረገም አብራርተዋል።

ግለሰቦችም ሆኑ ቀጣሪ ተቋማት ኤጀንሲዎች በህጋዊ መንገድ ስለመስራታቸው ካረጋገጡ በኋላ አስፈላጊውን ሂደት ተከትለው ግንኙነት ማድረግ እነደሚኖርባቸውም ሃላፊው አሳስበዋል።

netevm.com