የሐረር ጌይ ሞኦት (አለላ ስፌት) እና የጋምቤላ ሉል ዓለም አቀፍ ዕውቅና አገኙ

ሁለት የኢትዮጵያ የዕደ ጥበብ ምርቶች በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት (ብራንድ) መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በንግድ ምልክትነት የተመዘገቡት የዕደ ጥበብ ምርቶችም የሐረር ጌይ ሞኦት (አለላ ስፌት) እና የጋምቤላ ሉል ናቸው፡፡

የጋምቤላ ሉል የዕደጥበብ ውጤት

ምርቶቹን በንግድ ምልክትነት መመዝገባቸው ባለቤትነትን በማረጋገጥ ለማስጠበቅና ምርቶቹን ከፈጠራ መብት ስርቆት ለመታደግ እንዲሁም በዓለምአቀፍ ደረጃ የገበያ ትስስርን በመፍጠር ተሳታፊ ለመሆን እንደሚደራ የኢትዮጵያ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል ፡፡

የሐረር ጌይ ሞኦት (አለላ ስፌት) ምርት በሐረሪ ክልል በሰፊው የሚመረት ሲሆን በማህበረሰቡ ዕምነት፣ አኗኗር፣ ባህል፣ ልማድና ወግ ውስጥ የተለያየ ፋይዳ አለው የዕደጥበብ ውጤት ነው።

የጌይ ሞኦት 32 የሚደርሱ የአለላ ስፌት ዓይነቶች እንዳሉትና ከ34 ዓይነት በላይ ዲዛይን ያላቸው ስነ ጥበባዊ ገፅታን የተላበሱ፣ ለስጦታ እና ለመገልገያ የሚውሉ ባለጌጥ የስፌት አሰራርን የያዘ ነው ፡፡

የማህበረሰቡ የባህል መገለጫና ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር የተሳሰሩ በመሆናቸውና በአንድ የሐረሪ ሰው መኖሪያ ቤት የግድ መገኘት ስላለባቸው ምርቶቹ በማህበረሰቡ ዘንድ ልዩና ተፈላጊ መሆናቸውን የቅርስና ብህል ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ምዝገባ የምስክር ወረቅት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የጋምቤላ ሉል ምርት ደግሞ በክለሉ በብዛት የሚመረት የዕደጥበብ ውጤት ሲሆን ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውልና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ባህላዊ የዕደ ጥበብ ውጤት ነው፡፡

በሉል ምርት ከአካባቢው ኗሪዎች ባለፈ እምብዛም ያልተዋወቀ በመሆኑ ዕደጥበቡን ማስተዋወቅ እነደሚገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሩ ገልጸል።

የጋምቤላ ሉል ከባለቀለማት ቃጫ ገመድና የሳር ተክሎች የሚሰራ ዘምቢል መሰል አንዳነዴም በአነስተኛ ጀልባ ቅርስ የሚሰራ ዕቃ ማስቀመጫ ነው።

ምርቱን በዲዛይንና በደረጃ በማሻሻል የዕደጥበብ የምርቱን መለያ (ብራንድ) ምልክት በማዘጋጀት፣ በማልማት፣ በመጠበቅ ከምርቱ የሚገኘውን ጠቀሜታ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.