የራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሹመት

  • ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዩንቨርስቲው ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

Firehywot Tamru , CEO of Ethio telecom

Ethiopia | ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ቴሌኮም ወና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቦርድ ሊቀመንበርነት ሆነው ተሹመዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ሹመት ማግኘታቸው ታውቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ዓም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን አስረድተዋል።

netevm.com