የሰላም ውይይቱ ውጤት ያስገኝ ይሆን?

ከሶስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የእርስ በዕርስ ጦርነት በርካታ ጥፋቶችን አስከትሏል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ( ሕወሃት) ተወካዮች ይህንን ዓመታትን ያስቆጠረና ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆነ ጦርነት ለማስቆም በደቡብ አፍሪካ እየተወያዩ ነው።

አራተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውይይት የቀድሞው የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ሌላኛው የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳብጆ መሪነት እየተከናወነ ይገኛል። በአፍሪካ ሕብረት ስር በሚከናወነው ውይይት ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ተገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ይታወቃል።

በጦርነቱ ሕይወታቸው ካጡ ዜጎች ባለፈ በርካታ የጤና ተቋማት ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የተለያዩ የሕዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶች፣ የሐይማኖት ተቋማትና የተለያዩ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ይህን ደም አፋሳሽ ግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እየተደረገ ያለው ጥረት በብዙ ጫናዎች መካከል እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየገለጹ ነው።

መንግስት ወደመቀሌ የሚያደርገውን ግስጋሴ በቀጠለበት ወቅት የሕወሃት ሰዎች ወደሰላም ስምምነት የማይመጡበት ምክንያት እንደሌለ የሚገልጹ የፖለቲካ ምሁራን በርካታ ናቸው።

የህወሃት አመራሮች በበኩላቸው በስምምነት ስም ወደሌላ አገር ሊኮበልሉ ይችላሉ በሚል የተለያዩ ጥርጣሬዎች እየተነሳባቸው ይገኛል።

ያም ሆነ ይህ ሰላም ለሚፈልገው ሰፊው ሕዝብ ሲባል መግባባት ላይ መድረስ ቢቻል አሊያም መንግስት ሙሉ በሙሉ የትግራይ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማድረስ የሚችልበት መንገድ እንዲፈጸር የሚመኙ ዜጎች ግን በርካታ ናቸው።    

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.