የቤት ፈረሳ ላይ ያተኮረው የኢሰመኮ ሪፖርት

EHRC
Human rights commission report on Addis Ababa Schools

በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ
ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርቱን አቅርቧል።
ሕገ ወጥ ግንባታን የማፍረስ እርምጃ ሕጋዊ ሂደትን መከተልና እርምጃው ሊያስከትል
የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት አማራጭ መፍትሔዎችን ማመቻቸት
ያስፈልጋል ሲል መክሯል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ በቅርቡ በአዲስ መልክ በተደራጀው የሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ እና በግዳጅ ማስነሳት (Demolition and Forced Eviction) እየተከናወነባቸው ካሉ አካባቢዎች መካከል ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ መነ አብቹ እና በዙሪያው ከሚገኙ አካባቢዎችቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች በግል እና በቡድን ለኮሚሽኑ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ ከየካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህም መሠረት ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ሰዎችን፣ የሚመለከታቸውን የከተማ አስተዳደር እና
የጸጥታ አካላት በማነጋገር፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ቤቶችን የማፍረስ እና
በግዳጅ የማስነሳት ሂደቱ የሚከናወንበትን ሁኔታ እንዲሁም ቀደም ሲል የፈረሱ ቤቶችን
የመስክ ምልከታ በማድረግ ኢሰመኮ መረጃ እና ማስረጃ አሰባስቧል፡፡

ለኢሰመኮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ሰዎች ለኮሚሽኑ ሲያስረዱ በየአካባቢው ከቀድሞ/ነባር ባለ
ይዞታዎች ቦታ ወይም ቤት በመግዛት ኑሮ መሥርተው ሲኖሩ የነበሩ መሆናቸውን፣
በየአካባቢው ከሚገኙ ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የውሃ እና የመብራት አገልግሎት
ተጠቃሚ የነበሩ መሆናቸውን፣ ለተለያዩ የአካባቢው የልማት ሥራዎች እንደ ማንኛውም
ማኅበረሰብ ክፍያዎችን ሲከፍሉ መቆየታቸውን በመጥቀስ መኖሪያ ቤቶቻቸው ያለ በቂ ቅድመ
ማስጠንቀቂያ ከሕግ አግባብ ውጭ እንደፈረሱባቸው ይገልጻሉ።

ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የሸገር ከተማ ኃላፊዎች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ እንደ አዲስ
መመሥረቱን ተከትሎ “ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸውን” ግንባታዎች በማፍረስ ላይ
እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ሙሉውን ሪፖርት ያግኙ

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.