የአባይ ግድብ አራተኛ ዙር ውሀ ሙሌት

የአባይ ግድብ አራተኛና የመጨረሻ የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐ


የአባይ ግድብ አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ዛሬ ማለዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት፤ ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል።

ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር። በውስጥ ፈተና በውጭ ጫና ነበረብን። ከፈጣሪ ጋር የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚህ ደርሰናል ብለዋል።

የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም። በቀጣዩ ጊዜ ያቀድነውን አጠናቅቀን ፈጣሪን እንደምናመሰግን እምነቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።

netevm.com