የኢትዮጵያና ሜክሲኮን የ73 ዓመታት ግንኙነት የሚዘክረው አውደርዕይ

አዲስ አበባ በሚገኘው የዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር 8 ፣ 2015 ዓ.ም ምሽቱን የተከፈተው አውደርዕይ የኢትዮጵያንና የሜክሲኮን 73 ዓመታት ያስቆጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት ያደረገ አውደዕይ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል።

የፎቶ አውደርዕዩን ዳሸን ባንክ ከሜክሲኮ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።


በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ፣ የዳሽን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የልጅ ልጆች፣ የተለያዩ አገራት ኤምባሲ ተወካዮች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በፎቶ አውደርዕዩ የአፄ ኃይለሥላሴ የሜክሲኮ ጉብኝትን የሚያሳና ሜክሲካውያን በኢትዮጵያ ያላቸውን ቆይታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ተካተዋል።

በሜክሲኮ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ላይ የሚያጠነጥኑና የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።

ኢትዮጵያና ሜክሲኮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያ በጣሊያን ዳግም በተወረረችበት ወቅት ሲሆን በጊዜው ሜክሲኮ ወረራውን በመቃወም በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድምጿን በማሰማት ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን አሳይታለች።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አፄ ኃይለስላሴ በ1954 ሜክሲኮን በመጎብኘት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ መሠረት እንዲይዝ አደረጉ።

አውደርዕዩ በተከፈተበት ወቅት የውጭ ጉዳይ ዳይሬክተር የሜክሲኮ አምባሳደርና የዳሸን ባንክ ኃላፊ

በወቅቱ በሜክሲኮ በኢትዮጵያ ሥም አደባባይ የተሰየመ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም በሜክሲኮ ሥም አደባባይ በአዲስ አበባ ውስጥ በመሰየም ሀ ብሎ ለጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ታሪካዊ አሻራ አስቀመጡ።

አሁን ላይ ሜክሲኮ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት በማሳደግ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች በትብብር እየሰራች ይገኛል።

በተለይም ሁለቱ አገራት የህገወጥ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን በመከላከል ረገድ የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ እያከናወኑ መሆኑን ቀደም ብለው አስታውቀዋል።

በዳሸን ባንክ የተከፈተው የፎቶ አውደርዕይ የኢትዮጵያ ንና የሜክሲኮን 73 ዓመታት የተሻገረ ወዳጅነት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አላማ ማድረጉን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል።

ታሪካዊና ዘመን አይሽሬ ፎቶግራፍፎችን የያዘው አውደርዕዩ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ዳሸን ባንክ አስታውቋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.