የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ሊሰጥ ነው

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

መውጫ ፈተና በሁሉም መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ መርሐ-ግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከት እና ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር  ሳሙኤል ክፍሌ ገለጹ።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች ባሻገር የማታ እና የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከትም ገልጸዋል።

ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግሥት እና ለግል ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ እደገለጹት፣ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለሚማሩ የቀን፣ የማታና የርቀት መርሐ-ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ጠቁመዋል።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና  በበኩላቸው፣ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር  የተማሪዎችን እና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ በመውጫ ፈተና ዙሪያ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት፣ የመሠረተ ልማት እና የ2015 ምሩቃን መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.