የግብጽ ጠብ አጫሪ መግለጫና የኢትዮጵያ ማሳሰቢያ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የህዳሴ ግድብን በተመለከተ “ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው” በማለት የሰጡትን መግለጫ ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ሲል አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ግብጽ የዓባይ ግድብን አስመልክታ ለኢትዮጵያ ማስፈራሪያ የታከለበት መግለጫ ሰጥታለች ብሏል፡፡

ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ድንጋጌን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ይህ ድርጊት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ራሷኑ ግብጽና ሱዳን እ.አ.አ. በመጋቢት 2015 ያደረጉትን ስምምነት የጣሰም ነው ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው ገልጿል፡፡

በዚህም ግብጽ ተገቢ ያልሆኑና ህገወጥ መግለጫዎችን ከማውጣት እንድትቆጠብ አሳስቧል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የሚመለከታቸው አካላት ግብጽ የዓለም አቀፉ ግንኙነት ደንብን እየጣሰች መሆኗን ልብ ሊሉ ይገባልም ነው ያለው።

ግብፅ በማስፈራራትና ከህግ ውጭ ነገሮችን በማድረግ ፍላጎቷን ልታሳካ እንደማትችልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

ሆኖም በመከባበርና በመተማመን እንዲሁም የዓለም አቀፉን ህግ ባከበረ መልኩ ከሆነ ሀገራቱ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር መግባባት ላይ ይደረሳሉ የሚል ጽኑ እምነት እንዳለውም ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ አሁንም ሁሉም ወገን አሸናፊ እንዲሆን የሚል አቋማ ላይ እንደሆነችም አስታውቋል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.