የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም

ዛሬ በአዲስ አበባ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ስትራቴጂካዊ ግምገማ ተጀምሯል።

የሰላም ሂደቱ ወሳኝ ሁኔታዎች በተባሉት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎች እንዲበተኑ ማድረግ እና ከህብረተሰቡ ጋር መልሶ ማዋሃድ እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ግምገማ መካሄዱን የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽን አስታውቁዋል።

በመድረኩ

 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት 

 የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዛዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

 የቀድሞው የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 

 የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር

 የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ 

 የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ 

 የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ ይገኙበታል። 

 ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀመንበር)

 አቶ ጌታቸው ረዳ – የህወሓት ም/ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት

 ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ – የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት

 ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ -በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ተገኝተዋል::

netevm.com