የ157 ሰዎች የሞቱበት የቦይንግ 737 አውሮፕላን አደጋ ምርመራ

በ2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ አካባቢ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው፤ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ኢማክስ (EMACS) የተሰኘው የመቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ችግር መሆኑ ከ3 ዓመት በኃላ በምርመራ መረጋገጡ ተገለጸ።

የኢትዮጽያ የራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሥሩ ከሚገኘው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የአደጋውን የመጨረሻ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፉ አድርገዋል።

የምርመራ ቡድኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች፣ የአውሮፕላኑ አምራች ቦይንግ እና የአሜሪካ አቪዬሽን ባለሙያዎች መካተታቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ፤ የፈረንሳይና የአውሮፓ አቪዬሽን በምርመራው እንዲሳተፉ መደረጉንም አስረድተዋል።

የአደጋን የመጨረሻ ደረጃ ሪፖርት አስመልክቶ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፤ ምርመራው ዓለም አቀፍ ሂደቶችን ተከትሎ መካሄዱን ገልጸዋል።

በምርመራውም፤ የበረራ ሙያተኞቹ እና አውሮፕላኑ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ለበረራ ዝግጁ መሆናቸው የተረጋገጠ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ አውሮፕላኑ ለበረራ ሲነሳ የጭነት ክብደቱም ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዳልነበረ መረጋገጡን ገልጸዋል።

ለአደጋው መከሰት ዋነኛ ምክንያትም በአውሮፕላኑ ውስጥ የሚገኝው ኢማክስ (EMACS) የተባለ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ችግር መሆኑን ሚኒስትሯ አሳውቀዋል ።

መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩ አውሮፕላኑ አፍንጫውን ቁልቁል እንዲዘቀዘቅ ያደረገው ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ማድረጉን አስረድተዋል።

መሳሪያው የኤርፖርት እና የኤሌክትሮ ማግኔቲክ አካባቢ ትንተና እንዲሁም የአየር ማረፊያ እና የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጣቢያ ማረጋገጫን ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል።

መጋቢት 1 ቀን 2011 ከጠዋቱ 2:38 ደቂቃ ላይ መነሻውን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ መዳረሻውን ኬንያ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አድርጎ በረራ የጀመረው ET-302 ቦይንግ 737 – 8 ማክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መሬት በለቀቀ በ6ኛው ደቂቃ ላይ ቢሾፍቱ አካባቢ ልዩ ስፍራው ቱሉ ፎራ በተባለ ቦታ መከስከሱ ይታወሳል።

በአውሮፕላኑ ውስጥም ከ35 አገራት የተውጣጡ 149 ተሳፋሪዎች እንዲሁም 8 የበረራ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የ157 ሰዎች ህይወትም በአደጋው አልፏል።
በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቤተሰቦች ቦይንግ ኩባንያን ከሰውታል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.