የVisa Everywhere Initiative የፊንቴክ ውድድር በኢትዮጵያ ተጀመረ

 • Visa Everywhere Initiative ጀማሪ ቢዝነሶችን የወቅቱ አንገብጋቢ የሆኑ ክፍያዎችን እና የግብይት ተግዳሮቶችን እንዲፈቱ የገንዘብ ሽልማቶችን በመስጠት፤ በማስተዋወቅ እና አለም አቀፍ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ስምምነት እንዲኖር ለማስቻል ያበረታታል፡፡

Visa Everywhere Initiative የፊንቴክ ውድድር በኢትዮጵያ ተጀምሯል፡፡ ውድድሩ ጀማሪ ቢዝነሶች የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶችን ለመፍታት አዳዲስ መፍትሄዎችን እንዲያመጡ የሚያስችል ነው፡፡

የቪዛ መካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ፣ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ቢሮ ፕሬዝዳንት የሆኑት አንድሪው ቶሬ በቅርቡ ይህን ዜና ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በሰኔ ወር በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝታቸው ቪዛ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማስፋፋት ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና የፊንቴክ ፈጠራን ለማስፋፋት እና በሴቶች የሚመሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶችን ለማገዝ አዳዲስ ውጥኖችን እንዳሉት አሳውቀዋል፡፡

ይህም እቅድ በሀገር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የቪዛ ለሁሉም ፊንቴክ ውድድርን ለማዘጋጀት እና የቪዛን ‘ቀጣይ እሷ ናት’ የሴቶችን ማጎልበት ፕሮጀክት ማስጀመርን ያካትታል።

በ2013 የአሪፍፔይ የሽያጭ ክፍያ መነሻ ስርዓት አንደኛውን የቪዛ ለሁሉም ፊንቴክ ውድድርን አሸንፏል፡፡

‘የVisa Everywhere Initiative ለፊንቴክ እና ለስራ ፈጣሪዎች በክፍያ እና በንግድ አለም ላይ ተጨባጭ እና ውጤታማ መፍትሄዎችን እንዲያስገኙ የሚያስችል መድረክ ነው” ሲሉ የቪዛ የኢትዮጵያ ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ ተናግረዋል። ‘ፊንቴክ እና ሌሎች የክፍያ ስርአት ፈጣሪዎች ሸማቾች እና ነጋዴዎች ክፍያ የሚፈጽሙበትን መንገድ በመቀየር ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ገንዘብ በሚፈልጉበት ጊዜ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል። በ2013 በመጀመሪያው የቪዛ ለሁሉም ኢትዮጵያ ውድድር ወቅት በውድድሩ ባገኘናቸው ብዙ ተሳታፊዎች ተደንቀን ነበር፡፡ በዚህ ዓመትም ሌሎች አዳዲስ ችሎታ ያላቸው ተሳታፊዎችን እንጠብቃለን። በጋራ በመስራት ምቹ፣ አስተማማኝ እና እንከን የለሽ የክፍያ ስርአትን ለብዙዎች ተደራሽ ለማድረግ እንደምንችል እናምናለን።’

በአለም አቀፍ ደረጃ ይህ ፕሮጀክት ከ100 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ጀማሪ ንግዶች ከ2015 ጀምሮ ከ 16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያሰባስቡ ረድቷል ። የVisa Everywhere Initiative አውታረ መረብ ብዛት በአሁን ሰአት 12,000 ያህል ደርሷል፡፡

ከገንዘብ ሽልማቶች በተጨማሪ፣ የቪዛ ለሁሉም አሸናፊዎች ባንኮች፣ ነጋዴዎች፣ ቬንቸር ካፒታሊስቶች እና የመንግስት አካላት የሚገኙበትን የቪዛን ሰፊ የአጋሮች መረብ ውስጥ የመካተት እና የመታወቅ እድል ያገኛሉ። እንዲሁም አለምአቀፍ ከሆኑ እጅግ ታዋቂ ድርጅቶች እውቅናን ማግኘት ይችላሉ፨

የዘንድሮው የቪዛ ለሁሉም ኢትዮጵያ የፍፃሜ ውድድር በመስከረም ወር የሚካሄድ ሲሆን በድምሩ 50,000 ዶላር በተለያየ ደረጃ ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች የሚሰጥ ይሆናል። ይህም 1ኛ ደረጃ 25,000 ዶላር፣ 2ኛ ደረጃ 15,000 ዶላር እና 3ኛ ደረጃ 10,000 ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ::

የቪዛ ለሁሉም ኢትዮጵያ ውድድር ከታች የተጠቀሱትን ጨምሮ ንግዶች የሚያጋጥሟቸውን የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶች በመፍታት ማህበረሰቡን የሚያግዙ እና በሁሉም ዘርፍ እና ደረጃ የሚገኙ አዳዲስ እና ትልቅ ስራ ፈጣሪዎችን ይፈልጋል።

በስነ-ምህዳር ዘርፍ

 • ግብርና
 • ሎጂስቲክስ
 • የጤና ጥበቃ
 • ትምህርት
 • የከተማ ተንቀሳቃሽነት
 • ጊግ ኢኮኖሚ
 • ኢንሹራንስ

ዲጂታል ማረጋገጫ

 • የገንዘብ ማስተላለፍ እና ሬሚታንስ
 • ዲጂታል ዋሌት  P2P, እና ማስተላለፊያ
 • አማራጭ የብድር አገልግሎት

የፋይናንስ እሴትን ለነጋዴዎች እና/ወይም ሸማቾች መጨመር

 • መረጃ እና ትንታኔዎች
 • የጅምላ ቴክኖሎጂ

ለአነስተኛ እና መካከለኛ ንግዶች የሚያስፈልጉ መፍትሄዎች

 • የገንዘብ ድጋፍ
 • አዳዲስ ደንበⶉች እና ገበያዎች
 • አነስተኛ እና መካከለኛ ንግዶች በዕቃ አያያዝ፣ በደመወዝ ክፍያ ሂደት፣ በደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር ብቻ የተገደቡ እንዳይሆኑ ማስቻል

የቪዛ ለሁሉም ውድድር ምዝገባ የሚጠናቀቀው ነሀሴ 14 ይሆናል፡፡ ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ፡ https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-initiative/initiative.html    

netevm.com