ዳሸን ባንክ እስከ 700 ሺህ ብር የሚደርስ ዘመናዊ የዱቤ አገልግሎቱን “ዱቤ አለ” የተሰኘ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግብይት አገልግሎት አቅርቧል።
ባንኩ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ያበለጸገው “ዱቤ አለ” የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ በይፋ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።
የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስፋው አለሙ በወቅቱ እንደገለጹት ፤ ዳሸን ለዘመናዊ የግብይት ስርዓትን ለማስፋፋት ያላውን ጽኑ ፍላጎት በየጊዜው እያሳደገ አዳዲስ አሰራሮችንም ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
ባለፉት ጊዜያት በቴሌብር አማካኝነት ሰንዱቅ እንደኪሴና መላ የተሰኙ የብድር አገልግሎቶችን በመኛቅረብ ለበርካቶች ፈጣን ምላሽ የፋይናንስ አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁንም ዳሸን ባንክ በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ የዱቤ ግብይት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አስተማማኝ የባንክ አሰራር በማገዝ ሸማቾች በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ገዝተው ቆይተው መክፈል የሚችሉበትን አሰራር አስተዋውቋል ብለዋል።
ዱቤ አለ በተሰኘው አገልግሎት ባንኩ ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ጋር በመተባበር ሸማቾች ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና እንዲገዙና በ3 ወር፣ በ6 ወርና በ12 ወር ውስጥ የሚመለስ ክፍያ እንዲፈጽሙ እድሉን ማመቻቸቱን አስረድተዋል።
በቴክኖሎጂ ታግዞ የመጣው የዱቤ አገልግሎት ቀደምን ስንሰራበት የነበረውን ልምድ በዘመናዊ መልክ ያቀረበ ነው። በገበያው ውስጥ ምርት እንዲገላበጥ፣ አገልግሎቶችም ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እና የንግድ ማህበረሰቡ ሽያጭ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርገዋል ያሉት ደግሞ የዋሪት ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትህትና ሙሉሸዋ ናቸው።
ዱቤ አለ የምርትና አገልግሎት አቅራቢዎች ለደንበኞቻቸው እጅግ አመቺ የሆነ የዱቤ አገልግሎት በማቅረብ ተመራጭነታቸውን እንዲያሳድጉም የተለያዩ ድርጅት ሃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተው ገለጻ አድርገዋል።
ኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕ ስቶር በማውረድ ለአገልግሎቱ መመዝብ እንደሚችሉ አሳውቋል።
ትናንትና በተካሄደው የዱቤ አለ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ቀድመው ወደመተግበሪያው ለተመዘገቡ 20 ደንበኞች ዳሸን ባንክ ለእያንዳንዳቸው የሁለት ሺህ ብር ሽልማት ሰጥቷል።