ፋና ብሮድካስቲንግና ዋልታ ሲዋሃዱ በፋና መጠሪያ ይጠቀማሉ

Fana Broadcasting media logo
Addis Walta media logo

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ በመዋሀድ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ በሚል መጠሪያ ለመጠራት ወስነዋል::

የውህደቱ አመቻች ኮሚቴ ለተመሳሳይ ዓላማ በተመሳሳይ ባለአክሲዮኖች የተቋቋሙት እነዚህ ማህበራት ውህደቱን የሚፈጽሙበት ዋነኛ ምክንያት የፋይናንስ፣ የሰው ሀይል፣ የቴክኖሎጂ እና የመሰረተ ልማት አቅምን በማቀናጀት የሀብት ብክነትን ለማስቀረት እና ትርፋማነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ በማሰብ መሆኑን አሳውቋል።

ማህበራቱ ውህደቱን የሚፈጽሙት በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 በወጣው አዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ መሰረት ሲሆን ሰፊ ጊዜ በመውሰድ የውህደት እቅድ አዘጋጅተው በማህበራቱ የተናጠልና የጋራ ጠቅላላ ጉባኤዎች በሙሉ ድምጽ ማጽደቃቸውም ታውቋል::

የውህደቱ ሂደት በህግ መሰረት የሚመራ፣ የባለሀብቶቹን እና የ3ኛ ወገኖችን ጥቅም ባከበረ መልኩ መፈጸሙን የሚከታተሉ
ገለልተኛ ገምጋሚ ባለሙያዎችን መድበው ሲከታተሉ ቆይተዋል፣ የውህደት ሂደቱ ሪፖርትም ቀርቦ ፀድቋል::

የማህበራቱ የውህደት እቅድ፤ የማህበራቱ ጠቅላላ ጉባኤ የውህደት እቅዱን በሙሉ ድምጽ ያጸደቀበት ቃለ ጉባኤ እና
የገለልተኛ ገምጋሚ ባለሙያዎች ሪፖርት አዲስ አበባ፤ ልደታ ክ/ከ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ከሚገኘው የፋና
ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ህንጻ ውስጥ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።

በመሆኑም ውህደቱን በተመለከተ ጥያቄ አለኝ የሚል ባለመብት ጥያቄያቸውን ከላይ በተገለጸው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ
ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ለማቅረብ ይችላሉ ሲሉ አሳውቀዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 011-551-67-77 ወይም 011-550- 44-51 ደውሎ የውህደቱ አመቻች ኮሚቴን ማነጋገር እንደሚቻል ተጠቁሟል።

Ethiopian View Media Network- EVMN

netevm.com