9 ሀገራት የዓለም አቀፉን ድንበር ተሻጋሪ የንፋስ ኃይል ጥምረትን ተቀላቀሉ

በግብፅ ሻርም ኤል ሸክ እየተካሄደ በሚገኘው 27ኛው የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ተጨማሪ 9 ሀገራት የዓለም አቀፉን ድንበር ተሻጋሪ የንፋስ ኃይል ጥምረት መቀላቀላቸው ተሰምቷል፡፡

ጥምረቱን የተቀላቀሉት ዘጠኝ ሀገራትም አሜሪካ ፣ብሪታኒያ ፣ ቤልጂየም ፣ ኮሎምቢያ ፣ ጀርመን ፣ አየርላንድ ፣ ጃፓን ፣ ኔዘርላንድስ እና ኖርዌይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ሀገራቱ በአማራጭ የንፋስ ኃይል አቅርቦት ላይ በመሥራት የዓየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ያግዛሉ መባሉን የዓለም አቀፉን የታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ መረጃ አመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም የባህር ላይ የንፋስ ታዳሽ ኃይል አቅም ከ60 ጊጋ ዋት የዘለለ አይደለም።

የዓለም አቀፍ ታዳሽ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IRENA) እና የአለም አቀፍ ኢነርጂ ኤጀንሲ (አይኤአይኤ) የአለም ሙቀት መጠን 1.5 ዲግሪ እይጨመረ ያለበትን ሁኔታ ለመገደብ በ2050 የባህር ላይ የንፋስ ታዳሽ ኃይል አቅምን ከ2000 ጊጋ ዋት በላይ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ይጠበቃል።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.