9 ከተሞች በቀጥታ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ተጠሪ እንዲሆኑ ተወሰነ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው  መደበኛ  ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ 9 የክለሉ ከተሞች በቀጥታ ተጠሪነታቸው  ለክልሉ መንግስት እንዲሆኑ ወሰነ።

ለክልሉ መንግስት ተጠሪ የሆኑ ከተሞች

መቱ ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ ፣ ሸኖ ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌ ፣ ዶዶላና ሻኪሶ ከተሞች መሆናቸው ታውቋል።  

በተጨማሪ ምክር ቤቱ ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ እንዲደራጁ ውሳኔ አስተላልፏል

በውሳኔው መሰረት ቢሾፍቱ ከተማ ከአጎራባቹ ዱከም ከተማና ከሂዲ፣ ኡዴ ደንካካና ድሬ መዘጋጃ ቤት ከተሞች ጋር በመቀላቀል እንደሚደራጅ ታውቋል።

አዳማ ከተማ በበኩሉ የወንጂ ከተማን ጋር ሻሸመኔ ከተማ ደግሞ ከቢሻን ጉራቻ ከተማ ጋር በመቀላቀል መጀራጀቱ ይፋ ተደርጓል።

6ባቱ ከተማ ደግሞ ከአዳሚ ቱሉ ከተማ ጋር በአድ ላይ እንደሚመራ ተደርጓል።

በተጨማሪ ሮቤ ከተማና የጎባ ከተማ የተቀላቀሉ ሲሆን፤ ማያ ከተማ ከሀረማያ ከተማ፣ አወዳይ ከተማና የአዴሌ ከተማ ጋር መቀላቀሉ ታውቋል።

በሌላ በኩል መቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተደርጓል።

አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች በሬጂዮ ፖሊስ ከተማ የሚደራጁ ሲሆን የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ ወደዋና ከተማነት አድገዋል።

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል 21 ዞን አድርጎ የምስራቅ ቦረና ዞንን በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ይፋ አድርጓል። የዞኑ መቀመጫ  ነጌሌ ቦረና ከተማ ሆናለች።

netevm.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.